Menu Close

ዋና ገጽ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብረኤል ወቅድስት አርሴማ
Debre Bisrat WeKidist Aresema, Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

ወደ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ወቅድስት አርሴማ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ/ክ እንኳን በደህና መጡ!

“ጥበብ ሐነጸት ቤተ – ጥበብ ቤቷን ሰራች” እንኳን ወደ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ወቅድስት አርሴማ ገጽ በሰላም መጡ! ደብራችን ታኅሣሥ 18/2007 ወይንም December, 27/ 2014 በእግዚአብሔር ቸርነት በቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት አርሴማ አማላጅነት ተመሠረተ። ደብራችን ከተመሠረተ በኋላ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለምእመናን ከምታበረክታቸው መደበኛ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ልጆችን ውዳሴ ማርያምን ግብረ ዲቁና፣ የአማርኛ ቋንቋና የሥነ ምግባር ትምህርት በማስተማር ልጆቻችን ሃይማኖታቸውን እንዲያውቁ፣ ባሕላቸውን ቋንቋቸውን እንዲገነዘቡ ለማድረግ ከፍተኛ ሥራ ተሰርቷል። 17 ልጆችም ለማዕረገ ዲቁና በቅተዋል። የደብሩ ምእመናን በየጊዜው በሚያገኙት ተከታታይ የሃይማኖት ትምህርት በመንፈሳዊ እውቀታቸው እንዲበስሉ፣ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲጠነክሩ በማድረግ በንስሐ ሕይወት በሥጋ ወደሙ እንዲመላለሱ ላቅ ያለ ሥራ ተሰርቷል። በምእመናን ጥንካሬም በአጭር ጊዜ ውስጥ ግዙፍ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በመግዛት ሕዳር 8/2011 ዓ.ም (November18/2018) ቅዳሴ ቤቱ ተከብሮ አገልግሎት እየተሰጠበት ይገኛል። የልጆቻም ትምህርት ተስፋፍቶ በአሁኑ ሰዓት ከ180 በላይ ሕጻናት እየተማሩ ይገኛሉ። ይህንኑ የደብራችንን አገልግሎት ለማገዝ፣ በተለይም የልጆችን ትምህርት ለማጠናከር፣ እንዲሁ በሌላ ቦታ የሚገኙ ምእመናንን ዘመኑ ባመጣው ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ ለሙድረስ ታስቦ ይህ መካነ ድር ተዘጋጅቷል። መልካም ቆይታ ይሁንልዎ!!!